Mugher cement
አቢሲኒያ የኢንድስትሪ ሽልማት ድርጅት የተለያዪ ድርጅቶችን የአሸናፊዎች አሸናፊ ባዘጋጀው መርሀ ግብር ላይ የተለያዩ የክብር እንግዶች በተገኙበት በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል የሽልማት ዝግጅት መርሀ ግብር ላይ በርካታ ድርጅቶች ተሸላሚ ሲሆኑ ከነዚህ መካከል ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡት አንዱ የሆነው በኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ካስመዘገባቸው ውጤቶች ውስጥ ከጠንካራ ሰራተኞች፣ከፍተኛ አመራሮች መካከል የወርቅ ሜዳሊያና የዲፕሎማ ሽልማት ያስመዘገበ ሲሆን በተደረገው የሽልማት መስፈርት መሰረት የረጅም ዓመት አገልግሎትና ከፍተኛ ካፒታል ካስመዘገቡት መካከል 2ኛ በመውጣት የኢንድስትሪ ሽልማት ፕሮግራም ሀምሌ 14 ቀን 2016 ዓ.ም. የዋንጫ ተሸላሚ በመሆኑ የተሰማንን ደስታ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ ይህ ሽልማት በአጠቃላይ የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች ውጤት በመሆኑ የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ!!!
Latest Company News
የኮርፖሬሽኑ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ኢንጂነር ሁንዴሳ ደሳለኝ እና የፋይናንስ ዘርፍ ም/ዋና ሥራ አስፈጻሚ በሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የ3ኛ መስመር ፋብሪካ ላይ ያጋጠመውን ችግር በመጎብኘት ማኔጅመንቱ እና ሰራተኛው በጋራ በመሆን ችግሩን ለመፍታት እያደረጉ ያለውን ጥረት በማበረታታት ጥገናው በመረሃ ግብሩ መሰረት ተጠናቆ ወደ ሥራ በሚገባበት ሁኔታ ላይ ውይይት በማድረግ አቅጣጫ ሰጥተዋል፡፡Nov—-06/2024
ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ የ2016 ዓ.ም በጀት ዓመታዊ የዕቅድ አፈፃፀም ከመላው ሰራተኞች እና ማናጅመንት ጋር በመወያየት ዓመታዊ በአልን አክብሯል— Sep 7/2024
አንጋፋው ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ሲሚንቶን ከማምረት በተጨማሪ ብቃት ያለው የሰው ኃይል በማፍራት በሃገር ውስጥ ላሉ ሲሚንቶ አምራች ድርጅቶች የሰለጠነ የሰው ሃይል በማቅረብ ወደር የለሽ ፋብሪካ መሆኑ ይታወቃል፡፡
Recent Events
ለክቡራን ለደንበኞቻችን እና ባለድርሻ አካላት፡፡
በአሁኑ ወቅት የፋብሪካችን 1ኛ መስመር እየሰራና የሲሚንቶ አቅርቦቱ እንደቀጠለ ቢሆንም የ3ኛ መስመር ፋብሪካ ላይ ባጋጠመን ድንገተኛ ብልሽት ማኔጅመንቱ እና ሰራተኛው በጋራ በመሆን ጥገናውን በአጭር ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ወደ ማምረት ሥራ ለማስገባት ከፍተኛ ርብርብ በማድረግ ላይ መሆናችንን በትህትና እየገለፅን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ሙሉ ማምረት ሂደት የምንገባ መሆኑን በአክብሮት እንገልፃለን፡:Nov---4/2024
የሙገር ስሚንቶ ፋብሪካ የኩሳዬ ቡኡራ ቦሩ ት/ቤት በመገንባት
የሙገር ስሚንቶ ፋብሪካ በሸገር ከተማ መልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ በ2016 ዓ.ም የኩሳዬ ቡኡራ ቦሩ ት/ቤት በመገንባት የትምህርት ልማትን ለማሳደግ እና የትምህርት ጥራትን ለማሻሻል ላበረከተው ትልቅ አስተዎዕፆ እና ሌሎችም በተወጣው ማህበራዊ ተግባራት በዛሬ ቀን ማለትም መስከረም 02/2017 ዓ.ም የሸገር ከተማ በለገጣፎ ከተማ ባዘጋጀው ዕውቅና ፕሮግራም የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ገዛኸኝ ደቻሳ በፕሮግራሙ ላይ በመገኘት የሽልማት ዋንጫውን ተረክበዋል Sep---13/2024
Mugher Cement
Factory
Mugher cement Factory is a state owned factory established with a purpose of producing and supplying cement and carrying out related activities that are important for the attainment of its ….
Our social Footprint
Mugher Cement Factory performs different activities to fulfill corporate social responsibility of the surrounding kebeles. It supports the community on human and environmental protection, and social supports. In relation to transparency and accountability, the factory participate the administration, community and their representatives continuously to assure its sustainability.