RECENT EVENTS

አረንጓዴ አሻራ እና ቸግኝ ተከላ

የ2016 ዓ.ም ዙር ሃገር አቀፍ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር 7 ነጥብ 5 ቢሊዮን ችግኞችን በጋራ ለመትከል በተያዘው እቅድ መሰረት የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ በመልካ ኖኖ ክፍለ ከተማ እያሰገነባ በሚገኘው የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤት ጊቢ ውስጥ በኬሚካል ኢንዱስተሪ ኮረፖሬሽን ስር የሚገኙ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች፣ የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢ/ር ገዛኸኝ ደቻሳ እና የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮረፖሬሽን ዳይሬክተር ዶ/ር ኢ/ር ሁንዴሳ ደሳለኝ በተገኙበት ሃምሌ 15/2016 ዓ.ም የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር ተከናውኗል፡፡

ፋብሪካችን የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ተሸላሚ ሆኗል

አቢሲኒያ የኢንድስትሪ ሽልማት ድርጅት የተለያዪ ድርጅቶችን የአሸናፊዎች አሸናፊ ባዘጋጀው መርሀ ግብር ላይ የተለያዩ የክብር እንግዶች በተገኙበት በኢንተርሌግዠሪ ሆቴል የሽልማት ዝግጅት መርሀ ግብር ላይ በርካት ድርጅቶች ተሸላሚ ሲሆኑ ከነዚህ ድርጅቶች መካከል ከፍተኛ ውጤት ካስመዘገቡት ድርጅቶች አንዱና ብርቅዬ ፋብሪካችን ኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮርፖሬሽን ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ያስመዘገባቸው ውጤቶች ውስጥ ከጠንካራ ሰራተኞች፣ ቡድን መሪዎችና ከፍተኛ አመራሮች መካከል የወርቅ ሜዳሊያና የዲፕሎማ ሽልማት ያስመዘገበ ሲሆን ድርጅታችን በተደረገው የሽልማት መስፈርት መሰረት የረጅም ዓመት አገልግሎትና ከፍተኛ ካፒታል ካስመዘገቡት መካከል 2ኛ በመውጣት የኢንድስትሪ ሽልማት ፕሮግራም ሀምሌ 14 ቀን 2016 ዓ.ም. የዋንጫ ተሸላሚ በመሆኑ የተሰማንን ደስታ ለመግለፅ እንወዳለን፡፡ ይህ ሽልማት ውጤት የአንድና የሁለት ሰራተኛ ውጤት ብቻ ሳይሆን በአጠቃላይ የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች ውጤት በመሆኑ የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ሰራተኞች በሙሉ እንኳን ደስ አላችሁ እንኳን ደስ አለን!!!

የማህበራዊ ኃላፊነትን የመወጣት ልዩ ልዩ ሥራዎች

ትኩረት ለሴቶችና ሕፃናት ማህበር በዋናነት ተደራራቢ የጤና ችግር ያለባቸው አቅመ ደካማ ወላጆች ልጆችን በመንከባከብ ለሚሰጠው አገልግሎት ለሚያስገነባው ሕንፃ ብር 500000.00 /አምስት መቶሺህ/ በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት ሲሆን ለ2016 የዘመን መለወጫ በዓል 100 ለሚሆኑ ተደራራቢ የጤና ችግር ያለባቸው ሕፃናት አሳዳጊ አቅመ ደካማ እማወራ እና አባወራዎች ለእያንዳዳቸው አምስት ሊትር ዘይትና 10 ኪሎ ዱቄት እንዲሁም ለትንሳዔ በዓል 150 ለሚሆኑ ለእያንዳዳቸው 6 ሊትር ዘይት እና 10 ኪሎ ዱቁት በመለገስ በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ አጠቃላይ በብር 492040/ አራት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ አርባ/ ወጪ በማድረግ የማዕድ ማጋራት ሥራ ተሰርቷል። አንዴ ማማ የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ገቢ የሌላቸውን ሴቶች በቀላሉ ከወዳደቁ ወረቀቶች ሊሰሩ የሚችሉ ጌጣጌጦችን እና መገልገያ እቃዎችን ሊያመርቱ እንዲችሉ ስልጠና በመስጠት ገቢ እንዲያገኙ በማስቻል ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ፋብሪካው የተገለገለባቸውን ውድቅዳቂ ወረቀቶች እና ጊዜ ያለፈባቸውን ጋዜጦች እንዲሰጠው ጠይቆ በተፈቀደው መሠረት 438.10 ኪሎ.ግ ጋዜጣ እና የማያገለግሉ ወረቀቶች እንዲረከብ ተደርጓል::

‹‹ኢትዮጵያ ታምርት›› ባዛር በሚሊኒየም አዳራሽ

መንግሥት የኢንዱስትሪው ዘርፍ ችግሮችን ለማቃለል እየተገበራቸው ከሚገኙ የመፍትሔ ርምጃዎች መካከል ከሁለት ዓመት በፊት፣ ሚያዝያ 2014 ዓ.ም ይፋ የተደረገው የ‹‹ኢትዮጵያ ታምርት›› ሀገራዊ ንቅናቄ ተጠቃሽ ነው፡፡ በዚህ መሰረት አምራች ዘርፉን ያነቃቃው ‹‹ኢትዮጵያ ታምርት›› ባዛር በዛሬው እለት በሚሊኒየም አዳራሽ የተከፈተ ሲሆን በመክፈቻለው ላይ የመንግስት ከፍተኛ ሃላፊዎች እና የኬሚካል ኢንዱስትሪ ኮሮፖሬሽን ዋና ዳይሬክትር ዶ/ር ኢንጅነር ሁንዴሳ ደሳለኝ እና የሙገር ሲሚንቶ ፋበሪካ ዋና ስራ አስኪያጅ ኢንጅነር ገዛኸኝ ደቻሳ በመክፈቻው ላይ በመገኘት ለባለስልጣናት ሙገር ሲሚንቶ በሚያመርታቸው ምርቶች ላይ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡ ግንቦት
1/2016

የሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ ቮሊቦል ቡድን

ኩረት ለሴቶችና ሕፃናት ማህበር በዋናነት ተደራራቢ የጤና ችግር ያለባቸው አቅመ ደካማ ወላጆች ልጆችን በመንከባከብ ለሚሰጠው አገልግሎት ለሚያስገነባው ሕንፃ ብር 500000.00 /አምስት መቶሺህ/ በጥሬ ገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት ሲሆን ለ2016 የዘመን መለወጫ በዓል 100 ለሚሆኑ ተደራራቢ የጤና ችግር ያለባቸው ሕፃናት አሳዳጊ አቅመ ደካማ እማወራ እና አባወራዎች ለእያንዳዳቸው አምስት ሊትር ዘይትና 10 ኪሎ ዱቄት እንዲሁም ለትንሳዔ በዓል 150 ለሚሆኑ ለእያንዳዳቸው 6 ሊትር ዘይት እና 10 ኪሎ ዱቁት በመለገስ በዓሉን በደስታ እንዲያሳልፉ አጠቃላይ በብር 492040/ አራት መቶ ዘጠና ሁለት ሺህ አርባ/ ወጪ በማድረግ የማዕድ ማጋራት ሥራ ተሰርቷል። አንዴ ማማ የተባለ ግብረ ሰናይ ድርጅት ገቢ የሌላቸውን ሴቶች በቀላሉ ከወዳደቁ ወረቀቶች ሊሰሩ የሚችሉ ጌጣጌጦችን እና መገልገያ እቃዎችን ሊያመርቱ እንዲችሉ ስልጠና በመስጠት ገቢ እንዲያገኙ በማስቻል ለሚያደርገው እንቅስቃሴ ፋብሪካው የተገለገለባቸውን ውድቅዳቂ ወረቀቶች እና ጊዜ ያለፈባቸውን ጋዜጦች እንዲሰጠው ጠይቆ በተፈቀደው መሠረት 438.10 ኪሎ.ግ ጋዜጣ እና የማያገለግሉ ወረቀቶች እንዲረከብ ተደርጓል::

መዋለ ህፃናት ትምህርት ቤት ጉብኝት

ሙገር ሲሚንቶ ፋብሪካ በማህበራዊ ጉዳዮች ላይ በመሳተፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ በማድረግ ላይ ይገኛል፡፡ በዚሁ መሰረት እያደረጉ ከሉት ድጋፎች አንዱ የሆነው የሸገር ከተማ አስተዳደር መልካ ኖኖ ክ/ከተማ በማስገንባት ላይ ያለውን መዋለ ህፃናት ትምህርት ቤት የፋብሪካው ከፍተኛ ማኔጅመንት እና የሰራተኛ ማህበር ተወካዮች በመጎብኘት የፕሮጀክቱን አፈፃፀም የታየ ሲሆን ቀሪ የግንባታ ስራዎች በአፋጣኝ ተጠናቀው ወደ ስራ እንዲገባ በማኔጅመንቱ አቅጣጫ ተሰጥቶበታል፡፡ ግንቦት 1/2016

Scroll to Top